ፖሊዮ ቫይረስ በኦሮሚያ ክልል ማዕከላዊ ኦሮሚያ ዞን በአምቦ አካባቢ፣ እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በደራሼና ጎፋ ዞኖች ተከሠተ። ቫይረሱ ቀደም ሲል በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ፣ በኑዌር ዞን እና ኢታንግ ልዩ ወረዳ መከሠቱንም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገልጧል።
ፖሊዮ ቫይረስ በኦሮሚያ ክልል ማዕከላዊ ኦሮሚያ ዞን በአምቦ አካባቢ፣ እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በደራሼና ጎፋ ዞኖች ተከሠተ። ቫይረሱ ቀደም ሲል በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ፣ በኑዌር ዞን እና ኢታንግ ልዩ ወረዳ መከሠቱንም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገልጧል። ቫይረሱ በተከሠተባቸውና ለበሽታው ተጋላጭ በሆኑ አምስት ክልሎች ከ11 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን የሚያካትት የክትባት ዘመቻ ከኅዳር አጋማሽ ጀምሮ እንደሚካሄድ ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል። በዘመቻው በ120 የአዲስ አበባ ወረዳዎች 884 ሺሕ 323፣ በ81 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ወረዳዎች 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን፣ በ276 የኦሮሚያ ወረዳዎች 6 ነጥብ 8 ሚሊዮን፣ በ91 የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ወረዳዎች 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን፣ በ61 የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ወረዳዎች 661 ሺሕ 539 በድምሩ ከ11 ሚሊዮን በላይ…
Read the full story at addis_news ↗