አሳዛኝ ዜና‼️
አሳዛኝ ዜና‼️ ዛሬ ህዳር 5/2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከደምበል አደባባይ ወደ ጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9፣ ከደምበል ወደ መስቀል ፍላወር በሚያመራው መንገድ ላይ በሚገኘው ጋዜቦ አደባባይ አካባቢ ኅዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ገደማ በደረሰ የሥራ ላይ አደጋ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተረጋገጠ። አደጋው የደረሰው ሠራተኞቹ በግንባታ ላይ ባለ አንድ ሕንጻ ላይ የዕለት ሥራቸውን በማከናወን ላይ ሳሉ፣ ቆመውበት የነበረው ርብራብ በድንገት በመፍረሱ ከ12ኛ ፎቅ ላይ በመውደቃቸው ነው። በስፍራው የነበሩ ነዋሪዎችና መንገደኞች በድንገተኛው ክስተት ከፍተኛ ድንጋጤና ሐዘን ውስጥ መውደቃቸው ተገልጿል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት…
Read the full story at addis_reporter ↗