በጎሳ ግጭት የምትታመሰው ደቡብ ሱዳን ምርጫዋን አራዘመች!!
በጎሳ ግጭት የምትታመሰው ደቡብ ሱዳን ምርጫዋን አራዘመች!! የደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንታዊና የሕዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት አባላት ምርጫ መራዘሙን የሐገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል። ምርጫው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር የፊታችን ታሕሳስ 22 ቀን 2026 ሊካሄድ ቀን ተቆርጦለት ነበር። የደቡብ ሱዳን የምርጫ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጆሰፒን አቺሮ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንዳሉት ምርጫው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በየካቲት 11 ቀን 2027 ይካሄዳል። ምርጫው ለመጓተቱ ከጠቀሷቸው ምክንያቶች ባለው የፀጥታ ችግር የምርጫ ቁሳቁሶች ወደ መላ ሀገሪቱ ማዳረስ አለመቻሉና በየጊዜው የሚካሄዱ የጎሳ ግጭቶች ይገኙበታል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2011 ነጻነቷን ያወጀችው ደቡብ ሱዳን በፕሬዚደንት ሳል ቫኺርና ምክትላቸውና ተቃዋሚያቸው ሪክ ማቻር በተፈጠረ ውዝግብ እስከአሁን መረጋጋት ርቋት…
Read the full story at addis_news ↗