የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የግሉ ዘርፍ እና የውጭ አጋርነት ተሳትፎን ያካተቱ ሁለት አዳዲስ ኢንቨስትመንት ባንኮችን ወደ ገበያው አስገብቷል።

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-11-14 15:28:10 UTC
AdYour ad here[email protected]

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የግሉ ዘርፍ እና የውጭ አጋርነት ተሳትፎን ያካተቱ ሁለት አዳዲስ ኢንቨስትመንት ባንኮችን ወደ ገበያው አስገብቷል። ባለስልጣኑ ከሰፊ የፈቃድ ማመልከቻ ግምገማ ሂደት በኋላ ለኤ ኤም ጂ (AMG) ኢንቨስትመንት ባንክ ኃላ/የተ/የግ/ማ እና ለናይልብሪጅ (NileBridge) ኢንቨስትመንት ባንክ ኃላ/የተ/የግ/ማ የኢንቨስትመንት ባንክነት ፈቃድ መስጠቱ ታውቋል። ከፈቃድ አሰጣጡ ጎን ለጎን የሁለቱን አዳዲስ ተቋማት የ8 ተሿሚ እንደራሴዎች እና የ10 የቦርድ አባላት ሹመትንም አጽድቋል። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጀነራል ዳግማዊት ሽፈራው፣ በባለስልጣኑ ፈቃድ የተሰጣቸው አጠቃላይ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች ቁጥር 23 መድረሱን የኢንቨስትመንት ባንኮች ቁጥርም ወደ 11 ከፍ ማለቱን ገልጸዋል። እስካሁን ፈቃድ ከተሰጣቸው ኢንቨስትመንት ባንኮች መካከል…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]