ከስኳር ህመም ጋር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን 70 በመቶ ያህሉ ህመሙ እንዳለባቸው አያውቁም ተባለ
ከስኳር ህመም ጋር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን 70 በመቶ ያህሉ ህመሙ እንዳለባቸው አያውቁም ተባለ 👉የዓለም አቀፍ የስኳር ህመም ቀን በዓለም ለ35ኛ ጊዜ ተከበረ 35ኛው የዓለም አቀፍ የስኳር ህመም ቀን «በስኳር ሕመም ላይ ቀድመን እርምጃ እንውሰድ» በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተከብሯል። በኢትዮጵያ ከስኳር ህመም ጋር ከሚኖሩ ሰዎች መካከል 70 በመቶ ያህሉ ህመሙ እንዳለባቸው እንደማያውቁ የኢትዮጵያ የስኳር ህመም ማኅበር ፕሬዚዳንት ዶክተር ጌታሁን ታረቀኝ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። ህመሙ እንዳለባቸው ከታወቀባቸው ሰዎች መካከል መድኃኒት የሚወስዱት ከ20 በመቶ በታች ሲሆኑ በአግባቡ መቆጣጠር የቻሉት ደግሞ ከ4 በመቶ እንደማይበልጡ ተገነግሯል። የስኳር ህመም በዓለም ዙሪያ ስርጭቱ እየጨመረ ከመጡ የጤና ችግሮች መካከል አንዱ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። በ2024…
Read the full story at zena24now ↗