በጄኔቫ ኤርትራዊያን ‹‹ጦርነት ይቁም›› የሚል ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ፡፡ በዛሬው እለት በጄኔቫ ከተማ ከተለያዩ የአውሮፓ ክፍሎች የተሰባሰቡ ኤርትራዊያን ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ተገለፀ፡፡
በጄኔቫ ኤርትራዊያን ‹‹ጦርነት ይቁም›› የሚል ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ፡፡ በዛሬው እለት በጄኔቫ ከተማ ከተለያዩ የአውሮፓ ክፍሎች የተሰባሰቡ ኤርትራዊያን ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ተገለፀ፡፡ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑት እነዚህ ኤርትራዊያን በዋነኝነት ‹‹ጦርነት ይቁም›› የሚል መሪ መፈክር የያዙ ቢሆንም የተለያዩ መልእክቶችንም አስተላልፈዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል የኤርትራ ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት ይከበር፣ አለም አቀፍ ህግ ይከበር፣ ዲፕሎማሲና ውይይት ይቅደም የሚሉ ይገኙበታል፡፡ እንዲሁም የተባበሩት አረብ ኤመሬትስን የሚያወግዙ መፈክሮችም ተሰምተዋል፡፡ የኤርትራን ባንዲራና የፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂን ፎቶ አንግበው ይህንን ሰልፍ ባካሄዱት ኤርትራዊያን መሀል የኢትዮጵያን ባንዲራ የያዙ ጥቂት ሰዎችም ታይዋል፡፡ @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Read the full story at addis_reporter ↗