👏
👏 🇨🇳 ቻይና የሰራችው "CE-25A" የተባለ የኤሌክትሪክ አውሮፕላን በአብራሪዎች የመጀመሪያውን የሙከራ በረራ በስኬት አደረገ። አውሮፕላኑ የተሰራው በቻይና የንግድ አውሮፕላን ኮርፖሬሽን (COMAC) እና CATL በተባለው የባትሪ ኩባንያ ትብብር ነው። 19 ሰዎችን የመያዝ አቅም ያለው ይህ አውሮፕላን በሙከራው ወቅት ሁለት አብራሪዎችን እና አንድ መሐንዲስ ይዞ በአየር ላይ ለ16 ደቂቃ ያህል ቆይቷል። አውሮፕላኑ ለአጭር ርቀት የከተማ ለከተማ ጉዞዎች ተብሎ የተሰራ ነው። በአንድ ጊዜ የባትሪ ሙሌት እስከ 400 ኪሎ ሜትር መብረር ይችላል። ከዚህ ቀደም 19 ጊዜ ያለ አብራሪ ሙከራ አድርጎ ተሳክቶለታል። አሁን ላይ መንገደኞችን በመደበኛነት ማጓጓዝ እንዲጀምር የመንግስት ፈቃድ እየተጠባበቀ ይገኛል። ዥንዋ ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
Read the full story at tikvahethiopia ↗