የአዲስ አበባው የአድዋ ድልድይ መንገድ ተዘጋ
የአዲስ አበባው የአድዋ ድልድይ መንገድ ተዘጋ ለረጅም ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው የአድዋ ድልድይ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት መንገዱ መዘጋቱን ነው የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ያስታወቀው። በመንገዱ ላይ ያጋጠመው ችግር በጥናትና ዲዛይን የተደገፈ፣ ዘላቂ መፍትሄ እስኪሰጠው ድረስ፤ ባለስልጣኑ ከሴቶች አደባባይ ወደ ባልድራስ ትራፊክ መብራት የሚወስደው መንገድ፤ ከዛሬ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁለቱም አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ እንደሆነ እወቁልኝ ብሏል፡፡ በመሆኑም አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ባለሥልጣን መስሪያቤቱ ያሳስባል፡፡ @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Read the full story at addis_reporter ↗