የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ወታደራዊ ኃይሎች መጠናከርን ተከትሎ በባድሜ አካባቢ ሌሊቱን የድሮን እና የከባድ መሣሪያ ጥቃቶች መፈፀማቸው ተዘገበ
የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ወታደራዊ ኃይሎች መጠናከርን ተከትሎ በባድሜ አካባቢ ሌሊቱን የድሮን እና የከባድ መሣሪያ ጥቃቶች መፈፀማቸው ተዘገበ ለአዲስስታንዳርድ በስልክ አስተያየታቸውን የሰጡ ሁለት የአካባቢው ነዋሪዎች እንደተናገሩት፣ ድብደባው ረቡዕ ሌሊት ጀምሮ እስከ ሐሙስ ማለዳ የዘለቀ ሲሆን፣ የፍንዳታ እና የከባድ መሣሪያ ተኩስ ድምፆች ረፋድ ላይ መቀነሳቸውን ገልጸዋል። የጉዳዩን ሚስጥራዊነት ከግምት በማስገባት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት ዲፕሎማት «በሁለቱም ወገኖች ያለውን ከፍተኛ ወታደራዊ ዝግጅት በቅርበት ስንከታተል ነበር፤ ሆን ተብሎ የሚወሰድ ወይም በስሌት ስህተት የሚፈጸም እርምጃ ግጭት እንደሚቀሰቅስ ገምተን ነበር» ብለዋል። @Addis_News @Addis_News
Read the full story at addis_news ↗