አሜሪካ ያወጣችውን ማስጠንቀቂያ አደሰች‼

WASULIFEneutral2026-11-20 07:38:11 UTC
AdYour ad here[email protected]

አሜሪካ ያወጣችውን ማስጠንቀቂያ አደሰች‼ በኤርትራ ድንበር አቅራቢያ በሚገኙ የትግራይ አካባቢዎች የቀጠለውን ግጭት እና የጸጥታ ስጋት ተከትሎ፣ የአሜሪካ መንግሥት ዜጎቹ ወደ አፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች እንዳይጓዙ ኅዳር 10 ቀን ዳግም አሳሰበ። በተለይም በሰሜን አፋር እና ላሊበላን ጨምሮ በአማራ ክልል የሚገኙ ዜጎች ሁኔታዎች ሲመቻቹ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል። ዋሽንግተን ወደ ኢትዮጵያ የሚደረግ ጉዞን በድጋሚ እንዲያጤኑ በማሳሰብ የደረጃ 3 የጉዞ ማስጠንቀቂያዋን አጽንታለች። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሽሬ በረራ ቢጀምርም ወደ አክሱም የሚደረገው በረራ እንደተቋረጠ መቆየቱን ማሳሰቢያው አክሎ ገልጿል። ዋሱመሐመድ 👇👇👇👇👇👇👇👇 ቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ ድምፅ ለመስጠት https://creativeawards.et/nominees/wasu-mohammed-wasumohammed…

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]