የአሜሪካ የነዳጅ ክምችት በመጨመሩ የዓለም ነዳጅ ዋጋ ቅናሽ አሳየ
የአሜሪካ የነዳጅ ክምችት በመጨመሩ የዓለም ነዳጅ ዋጋ ቅናሽ አሳየ በአሜሪካ የድፍድፍ ነዳጅ እና የነዳጅ ውጤቶች ክምችት ከተጠበቀው በላይ መጨመሩን ተከትሎ፣ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ረቡዕ ዕለት ከ1 በመቶ በላይ ቅናሽ ማሳየቱን ሮይተርስ ዘግቧል። በዚህም መሠረት የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ1.19 ዶላር ወይም በ1.28 በመቶ ቀንሶ በበርሜል 91.95 ዶላር የተሸጠ ሲሆን፣ የአሜሪካው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዲየት ነዳጅ ደግሞ በ2.75 ዶላር ወይም በ3.2 በመቶ ቅናሽ በማሳየት በበርሜል 83.26 ዶላር ሆኗል። ይህ የኢንተርሚዲየት ዋጋ ከባለፈው ነሐሴ ወር መጨረሻ ወዲህ ዝቅተኛ ደረጃ ነው። የአሜሪካ ኢነርጂ መረጃ አስተዳደር ይፋ እንዳደረገው፣ እስከ ኅዳር 13 በነበረው ሳምንት የሀገሪቱ የድፍድፍ ነዳጅ ክምችት በ3.4 ሚሊዮን በርሜል ጨምሮ 417.8 ሚሊዮን በርሜል ደርሷል፤ የቤንዚን…
Read the full story at ayuzehabeshanews ↗