የፈንታሌ እሳተ ገሞራ ያለ ፍንዳታ ከፍተኛ መጠን ያለው ሚቴን እና ካርቦን ዳይኦክሳይድ ጋዝ ለቋል - ተመራማሪዎች
የፈንታሌ እሳተ ገሞራ ያለ ፍንዳታ ከፍተኛ መጠን ያለው ሚቴን እና ካርቦን ዳይኦክሳይድ ጋዝ ለቋል - ተመራማሪዎች በብሪስቶል ዩኒቨርሲቲ የተመሩ ሳይንቲስቶች በሳተላይት ምልከታ ያገኙት ይህ ክስተት ከፈረንጆቹ ከታህሳስ 2024 እስከ መጋቢት 2025 ባሉት ሶስት ወራት ውስጥ የተከሰተ ሲሆን፤ በዓይነቱ የመጀመሪያው ግዙፍ የእሳተ ገሞራ ሚቴን ልቀት መሆኑ ተረጋግጧል። ከአዲስ አበባ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ፈንታሌ ቢያንስ 38 ኪሎ ቶን ሚቴን እና 2.9 ሜጋ ቶን ካርቦን ዳይኦክሳይድ ወደ አየር ለቋል። ይህ መጠን በሌሎች እሳተ ገሞራዎች ከሚታየው በአስር ሺዎች እጥፍ የሚበልጥና ከትላልቅ የኢንዱስትሪ ፍንዳታዎች ጋር የሚስተካከል ነው። በኔቸር ጂኦሳይንስ መጽሔት ላይ የታተመው ጥናት እንደሚያሳየው፤ የዚህ ክስተት ዋና ምክንያት ከመሬት በታች የተከሰተ ግዙፍ የማግማ እንቅስቃሴ…
Read the full story at addis_news ↗