ህዳር ሲታጠን በሚል ቆሻሻ ከማቃጠል ህብረተሰቡ ሊቆጠብ ይገባል ተባለ

ZENA24NOWneutral2026-11-20 10:58:45 UTC
AdYour ad here[email protected]

ህዳር ሲታጠን በሚል ቆሻሻ ከማቃጠል ህብረተሰቡ ሊቆጠብ ይገባል ተባለ በኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት በህዳር 12 ቀን ከሚከበሩ ባህላዊ ልማዶች አንዱ ቆሻሻን በመሰብሰብ የማቃጠል ተግባር ነው። ሆኖም ይህ ልማድ በአየር ብክለት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከማድረጉም በላይ በሰው ጤናና በአካባቢ ላይ ጉዳት የሚያስከትል በመሆኑ ማህበረሰቡ ከድርጊቱ በመቆጠብ ዘመናዊና ተገቢ የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓትን ሊከተል እንደሚገባ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አሳስቧል። በባለስልጣኑ የስርዓተ ምድር አጠቃቀምና ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ተሬሳ ጨመዳ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት ይህም ድርጊት በህግ የተከለከለ ተግባር ቢሆንም አሁንም በዚሁ ድርጊት ላይ የሚሳተፉ ሰዎች እንዳሉ ገልፀዋል። ድርጊቱ በአካባቢ ብክለት ቁጥጥር አዋጅ መሠረት በገንዘብ ቅጣትና በእስራት የሚያስቀጣ መሆኑን የጠቆሙት…

Read the full story at zena24now ↗
AdYour ad here[email protected]