ሳውዲ የሚሳኤል ጥቃት ደረሰባት‼
ሳውዲ የሚሳኤል ጥቃት ደረሰባት‼ በሪያድ 'ኪንግ አብዱላህ የፋይናንስ ማዕከል' የሚገኘው የሳዑዲ የሕዝብ ኢንቨስትመንት ፈንድ (PIF) ባለ 80 ፎቅ ሕንፃ፣ በሁቲዎች በተተኮሰ የሚሳኤል ጥቃት ጉዳት ደረሰበት። በጥቃቱ ምክንያት በሕንፃው እና በአቅራቢያው ባሉ ሕንፃዎች ላይ ቁሳዊ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ ምንም ዓይነት የሰው ሕይወት መጥፋትም ሆነ የመቁሰል አደጋ አለመድረሱን የሳዑዲ ሲቪል መከላከያ አስታውቋል። አደጋውን ተከትሎ ማዕከሉ ለጎብኚዎች ዝግ ሆኗል። ሮይተርስ ሕንፃው በቀጥታ በሚሳኤል መመታቱን ሲዘግብ፣ በሳዑዲ የሚመራው ጥምር ጦር በበኩሉ ጉዳቱ የደረሰው ጥቃቱን ለማክሸፍ በተደረገ ሂደት በወደቀ የሚሳኤል ስብርባሪ መሆኑን ገልጿል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት በማዕከሉ ላይ የተፈጸመ ሁለተኛው ጥቃት መሆኑን ተከትሎ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ ሉዓላዊነቷን ለመጠበቅ ተገቢውን እርምጃ የመውሰድ…
Read the full story at wasulife ↗