በሩሲያ የሚሳኤል ጥቃት በኪየቭ ሦስት ድልድዮች ተመቱ
በሩሲያ የሚሳኤል ጥቃት በኪየቭ ሦስት ድልድዮች ተመቱ ሩሲያ በሌሊት በፈጸመችው ከባድ የሚሳኤልና የድሮን ጥቃት በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ የሚገኙ ሦስት ድልድዮችንና የባቡር ጣቢያዎችን ኢላማ አድርጋ መምታቷ ተገልጿል። ጥቃቱ የተፈጸመው ዩክሬን ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለውን የክራይሚያን ድልድይ ክፉኛ ከጎዳች ከጥቂት ቀናት በኋላ ሲሆን፣ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የክሬምሊን አጸፋዊ ምላሽ «እጅግ ከባጅ ይሆናል» ሲሉ ዝተው ነበር። የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ «ከተፈጸሙት ግዙፍ ጥቃቶች አንዱ» ባሉት በዚህ ጥቃት ቢያንስ ስምንት ሰዎች ተገድለዋል። ከዚህ በተጨማሪም በዘጠኝ ክልሎች በደረሰው ጥቃት 28 ሰዎች መቁሰላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ሰርሂ ኮሬትስኪ ገልጸዋል። በሚኪያስ ጸሐዬ #ዳጉ_ጆርናል
Read the full story at zena24now ↗