🤖 🇨🇳 በቻይና ቻንግሻ ከተማ ሰው መሰል ሮቦት የትራፊክ ፖሊስ ሆኖ ተሰማርቷል።

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-11-21 00:01:19 UTC
AdYour ad here[email protected]

🤖 🇨🇳 በቻይና ቻንግሻ ከተማ ሰው መሰል ሮቦት የትራፊክ ፖሊስ ሆኖ ተሰማርቷል። ይህ ሮቦት ከትራፊክ መብራቶች ጋር በተቀናጀ መልኩ የእጅ ምልክቶችን በመጠቀም አሽከርካሪዎችን የሚመራ ሲሆን የራስ መከላከያ (ሄልሜት) ላላደረጉ የኤሌክትሪክ ብስክሌት ነጂዎች የድምፅ ማሳሰቢያ ይሰጣል፤ እንዲሁም ወደ መኪና መንገድ የሚገቡ ብስክሌተኞችን ያስጠነቅቃል። በሀገር ውስጥ በተመረቱ ቺፖች የተገጠመለት ይህ ሮቦት የቅኝትና የትራፊክ ቁጥጥር መደበኛ ሥራዎችን በራሱ ማከናወን ይችላል። እንደ አደጋ እና አለመግባባት ያሉ ውስብስብ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ግን ለተጨማሪ እርዳታ ለሰው ፖሊስ ሪፖርት ያደርጋል። @tikvahethiopia

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]