አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት⚠️⚠️

AYUZEHABESHANEWSneutral2026-11-21 10:27:26 UTC
AdYour ad here[email protected]

አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት⚠️⚠️ የሲቢኢብር የብድር አገልግሎት በሚል የተከፈተ ሀሰተኛ ድረ-ገፅ በማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተሰራጨ ስለሚገኝ ደንበኞች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ የጥንቃቄ መልዕክት ተላልፏል። ጥቃት አድራሾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለማስያዣ የሚሰጠው የሲቢኢብር ዲጂታል የብድር አገልግሎት መስጫ/ማመልከቻ በማስመሰል ባበለጸጉት ድረ-ገፅ፣ እንደ ስልክ ቁጥር፣ የይለፍ ቃል፣ ለማንነት ማረጋገጫ የሚላከውን የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል (One-time password (OTP)) የመሳሰሉ የደንበኞችን ሚስጥራዊ መረጃዎች ለመመንተፍ እየሞከሩ መሆኑ ተደርሶበታል። ጥቃት አድራሾቹ የፈጠሩትን ሀሰተኛ ድረ-ገጽ (https://cbe-loanxxxxx) እንደ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ዋትስአፕ፣ በመሳሰሉ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በስፋት እያሰራጩ የሚገኙ ሲሆን፣ ከተያያዙት ምስሎች ለማየት…

Read the full story at ayuzehabeshanews ↗
AdYour ad here[email protected]