የውጭ ባንኮች የሀገር ውስጥ ባንኮችን 100% እንዲገዙ የሚፈቅድ ረቂቅ መመሪያ መውጣቱ ተሰማ‼

WASULIFEneutral2026-11-21 10:31:34 UTC
AdYour ad here[email protected]

የውጭ ባንኮች የሀገር ውስጥ ባንኮችን 100% እንዲገዙ የሚፈቅድ ረቂቅ መመሪያ መውጣቱ ተሰማ‼ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ባንኮች ነባር የሀገር ውስጥ ባንኮችን በልዩ ሁኔታ እስከ 100 በመቶ እንዲገዙ የሚፈቅድ ረቂቅ መመሪያ አቀረበ፤ ይህም በአዋጁ የተቀመጠውን የ49 በመቶ ገደብ የሚያልፍ ነው። ሙሉ ግዢ የሚፈቀደው ትላልቅ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ ወይም በገንዘብ ችግር የወደቁ ባንኮችን ለማዳን ሲሆን፣ በኢንቨስትመንት መስክ የሚመጣው ባንክ ቢያንስ 10 ቢሊዮን ዶላር ሀብት፣ የ10 ዓመት ልምድ፣ በሦስት ሀገራት የሚሠራና ለሦስት ዓመት ትርፋማ መሆን ይጠበቅበታል። በችግር ላይ ያሉ ባንኮችን ለማዳን ለሚመጡት ግን የ10 ቢሊዮን ዶላሩ መስፈርት ሳይጠበቅ፣ ባንኩን የማቋቋምና የደንበኞችን ገንዘብ የመጠበቅ አቅማቸው ብቻ ተገምግሞ ፈቃድ እንደሚሰጣቸው ብር ሜትሪክ በዘገባው አመልክቷል።…

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]