የኤርትራ ኃይሎች በባድመ አቅራቢያ በሚገኙት ጓል ገምሃሎ እና ሰምበል መንደሮች ከፍተኛ ተጨማሪ ጦርና ከባድ ወታደራዊ መሣሪያዎች ማሰማራታቸውን ኤ.ኤፍ.ፒ ዘግቧል።
የኤርትራ ኃይሎች በባድመ አቅራቢያ በሚገኙት ጓል ገምሃሎ እና ሰምበል መንደሮች ከፍተኛ ተጨማሪ ጦርና ከባድ ወታደራዊ መሣሪያዎች ማሰማራታቸውን ኤ.ኤፍ.ፒ ዘግቧል። በተያያዘ ዜና በኢትዮጵያ በኩል ምሽጎች እየተቆፈሩ መሆናቸውን የሰብዓዊ ዕርዳታ ምንጮች ለኤ.ኤፍ.ፒ የገለጹ ሲሆን፣ በቡሬ-አሰብ ግንባር እስካሁን የጎላ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ባይኖርም የኤርትራ ኃይሎች ከቡሬ በሰሜን ምሥራቅ ሦስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በከፍተኛ ሁኔታ መሽገው እንደሚገኙ ተመልክቷል። ባለፉት ቀናቶች ውስጥ የህወሓት ጄኔራሎች እና የኤርትራ ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎች በኤርትራ ድንበር አካባቢ ተደጋጋሚ ስብሰባዎችን እያደረጉ እንደሚገኙ ተዘግቧል። አዩዘሀበሻ ======================== ለትክክለኛ ወቅታዊ መረጃ ቻናላችንን join አድርጉ፣ለትክክኛ መረጃ ፈላጊዎች ጋብዙ👇👇👇👇👇👇👇👇…
Read the full story at ayuzehabeshanews ↗