በረሮን እና አይጥን ያለ ከባድ ኬሚካል ለመቆጣጠር የሚረዱ የቤት ውስጥ እና የመከላከያ ዘዴዎች ይፋ ተደረጉ

ADDIS_NEWSneutral2026-11-21 11:34:01 UTC
AdYour ad here[email protected]

በረሮን እና አይጥን ያለ ከባድ ኬሚካል ለመቆጣጠር የሚረዱ የቤት ውስጥ እና የመከላከያ ዘዴዎች ይፋ ተደረጉ በረሮዎች እና አይጦች በጤና እና በምግብ ላይ የሚያስከትሉትን ጉዳት ለመከላከል፣ ቤተሰብን፣ ህፃናትን እና ምግብን ለከባድ ኬሚካሎች ሳያጋልጡ በቤት ውስጥ በሚገኙ ቀላል ነገሮች እነዚህን ተባዮች መቆጣጠር የሚቻልባቸው መንገዶች ተጠቆሙ። በረሮዎችን ለማጥፋት እና ለማባረር እኩል መጠን ያለው ቤኪንግ ሶዳ እና የተፈጨ ስኳር (1 ለ 1) በደረቁ ቀላቅሎ ከሲንክ ስር እና ከፍሪጅ ጀርባ በትናንሽ ክዳኖች ማስቀመጥ እንደሚቻል ተገልጿል። ስኳሩ በረሮዎችን ሲስብ ቤኪንግ ሶዳው ሆድ ውስጥ ካለው አሲድ ጋር በመዋሃድ ጋዝ በመፍጠር ያጠፋቸዋል፤ ሆኖም እርጥበት እንዳይነካው ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ነው የተባለው። በተጨማሪም 1 የሾርባ ማንኪያ ቦሪክ አሲድ፣ 1 የሾርባ ማንኪያ የስንዴ ዱቄት…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]