🕯 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የቀዶ ህክምና ትምህርት ክፍል ውስጥ በዩሮሎጂ (የሽንት ቱቦና ተያያዥ አካላት ህክምና) ስፔሻሊስትነት እና በተባባሪ ፕሮፌሰርነት ሲያገለግሉ የነበሩት ሀንጋሪያዊው ዶ/ር ሳሞዲ ላስሎ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ኮሌጁ እና ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።
🕯 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የቀዶ ህክምና ትምህርት ክፍል ውስጥ በዩሮሎጂ (የሽንት ቱቦና ተያያዥ አካላት ህክምና) ስፔሻሊስትነት እና በተባባሪ ፕሮፌሰርነት ሲያገለግሉ የነበሩት ሀንጋሪያዊው ዶ/ር ሳሞዲ ላስሎ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ኮሌጁ እና ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል። ዶ/ር ሳሞዲ በኢትዮጵያ የሁለት አስርት ዓመታት አገልግሎታቸው ወቅት የዩሮሎጂ ቀዶ ህክምና ዘርፍን በማዘመን ፣ የድህረ-ምረቃ ስልጠና ፕሮግራሞችን በመመስረት ፣ ክልኒካዊ ስልጠና በመስጠት ፣ የዩሮሎጂ እና ውስብስብ ህክምናዎችን በማከናወን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። የቀብር ስነ-ስርዓታቸው ትናንት ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም በየካ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል። ህዳር 12 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
Read the full story at tikvahethiopia ↗