ኢትዮጵያ የዓለም የሲቪል አቪዬሽን ምክር ቤት አባል ሆና ተመረጠች‼
ኢትዮጵያ የዓለም የሲቪል አቪዬሽን ምክር ቤት አባል ሆና ተመረጠች‼ ኢትዮጵያ 133 ድምፅ በማግኘት የዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ምክር ቤት አባል ሆና መመረጧ ተገለጸ። በካናዳ በተካሄደው ስብሰባ ኢትዮጵያ ከቱርክዬ፣ ከኦማን እና ከኢንዶኔዢያ ጋር የተመረጠች ሲሆን፤ ምክር ቤቱ ዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ሕጎችን፣ የበረራ ደህንነትንና የአየር ክልል ፖሊሲዎችን የሚያወጣ ዋና ውሳኔ ሰጪ አካል ነው። ይህ ውጤት ኢትዮጵያ ሌሎች ያወጡትን የበረራ ሕግ ተቀባይ ብቻ ከመሆን ወጥታ ሕጉን ከሚያረቁ አገራት ተርታ እንድትሰለፍ የሚያስችላት ሲሆን፣ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ለአገሪቱ ዲፕሎማሲና በአፍሪካ አቪዬሽን ዘርፍ ላላት መሪነት ትልቅ ዓለም አቀፍ ፋይዳ እንዳለው ተመልክቷል። ዋሱመሐመድ 👇👇👇👇👇👇👇👇 ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የቴሌግራም ቻናሉን…
Read the full story at wasulife ↗