ተወዳጁ ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ዛሬ በወልቂጤ ከተማ የሙዚቃ ሥራውን እያቀረበ በነበረበት ወቅት ባጋጠመው ድንገተኛ ሕመም ምክንያት ሕይወቱ ማለፉን የሙያ ባልደረባው ድምፃዊ ረሻድ ከድር ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተናግሯል።
ተወዳጁ ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ዛሬ በወልቂጤ ከተማ የሙዚቃ ሥራውን እያቀረበ በነበረበት ወቅት ባጋጠመው ድንገተኛ ሕመም ምክንያት ሕይወቱ ማለፉን የሙያ ባልደረባው ድምፃዊ ረሻድ ከድር ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተናግሯል። ድምጻዊ ሚኪያስ ቸርነት ፥ " ሰላም አላት " እና " 10/10 " የተሰኙ ሁለት ተወዳጅ አልበሞችን ለአድማጭ አቅርቧል። በተጨማሪ ድምጻዊው " የኔ ደሃ " ፣ " አሁን ገባኝ " ፣ " ቀረ ድሮ " ፣ " ዚዮዜ " ፣ " ግርማ ሞገሴ ነሽ " እና " ኪያዬ " በተሰኙና በሌሎችም ስራዎቹ በበርካታ የሙዚቃ አድማጮች ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፏል። ህዳር 12 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
Read the full story at tikvahethiopia ↗