የሲቢኢ ብር ብድር ማጭበርበር‼
የሲቢኢ ብር ብድር ማጭበርበር‼ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ሎጎ እና ገጽታ በመጠቀም የሲቢኢብር ብድር እና CBEbirr Plus መግቢያ የሚያስመስሉ ሀሰተኛ ድረ-ገጾች በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጩ ነው። አጭበርባሪዎች PIN እና OTP በመሰብሰብ አካውንቶችን ይጠልፋሉ፤ እንዲሁም የብድር 10% ቅድመ ክፍያ ይጠይቃሉ። ባንኩ የሲቢኢብር ብድር በድረ-ገጽ እንደማይሰጥ አስታውቋል። ደንበኞች አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን እንዳይከፍቱ፣ PIN እና OTP ለማንም እንዳያጋሩ፣ የይለፍ ቃል እንዲቀይሩ እና ችግር ሲያጋጥም ወዲያውኑ ወደ 951 እንዲደውሉ ተመክሯል። ዋሱመሐመድ 👇👇👇👇👇👇👇👇 ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
Read the full story at wasulife ↗