የኢትዮጵያ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ለተከታታይ አራተኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ ተባለ

ADDIS_NEWSneutral2026-11-22 07:46:34 UTC
AdYour ad here[email protected]

የኢትዮጵያ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ለተከታታይ አራተኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ ተባለ የኢትዮጵያ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በ2026 በተካሄደው የአረቢያን ካርጎ ሽልማት ላይ ለተከታታይ አራተኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አየር መንገድ ተብሎ ተሸልሟል። ይህ ሽልማት የኢትዮጵያ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በአህጉሪቱም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ፈጣን፣ ቀልጣፋና የጥራት ደረጃውን የጠበቀ የካርጎ ማጓጓዣ አገልግሎት በመስጠት ያለውን ተወዳዳሪነትና የላቀ አፈጻጸም የሚያረጋግጥ መሆኑ ተመላክቷል። ለተከታታይ አራት ዓመታት ይህንኑ ዕውቅና ማግኘቱም ተቋሙ በዓለም አቀፉ የካርጎ ማጓጓዣ ዘርፍ ያለውን ጠንካራ አቋም የሚያመለክት መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል። @Addis_News @Addis_News

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]