የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመርቋል።
የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመርቋል። ማዕከሉ በዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊ ሳይንስ፣ ስነ-ጥበባትና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ውስጥ የተቋቋመ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በቻይና የማኅበራዊ ሳይንስ አካዳሚ ትብብር የተቋቋመ መሆኑ ተገልጿል። ማዕከሉ በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት፣ በድህነት ቅነሳ፣ በሰላምና ደኅንነት እንዲሁም በዘላቂ ልማት ዘርፎች የጋራ ጥናቶችን በማካሔድ የምርምር ውጤቶቹን ለፖሊሲ ውሳኔዎች ግብዓት እንዲሆኑ የሚያደርግ መሆኑ ተመላክቷል። በቻይና እና በአፍሪካ ምሑራን መካከል የዕውቀትና የልምድ ልውውጥን ለማሳደግ ይሠራልም ተብሏል። ማዕከሉ ተከታታይ የምርምር፣ የውይይት፣ የስልጠና እና የባህል ልውውጥ የሚያካሒዱ ባለሙያዎችን በመለየት ወደ ሥራ ይገባል ተብሏል። @tikvahuniversity
Read the full story at tikvahuniversity ↗