26ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዛሬ በታላቅ ድምቀት ተከናወነ።
26ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዛሬ በታላቅ ድምቀት ተከናወነ። መነሻና መድረሻውን በመስቀል አደባባይ ባደረገው በዚህ የ10 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ላይ 60 ሺህ ህዝብ ተሳታፊ ሆኗል።የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አበቤ፣ በ5000 እና 10,000 ሜትር የፓሪስ ኦሎምፒክ የጥምር ድል ባለቤት የሆነችው ኬንያዊቷ ቢያትሪስ ቼቤት በክብር እንግድነት ተገኝተው ውድድሩን አስጀምረውታል። በታዋቂ አትሌቶች መካከል በተደረገው ውድድር ይስማው ድሉ ቀዳሚ ሆኖ በመግባት የአምና ድሉን ደግሞታል።ርቀቱን ለመጨረስም 28:33.9 ፈጅቶበታል። ታከለ ሞሴ (28:34.8) እና ከቤ መርጋ (28:36.1) ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘው አጠናቅቀዋል። በሴቶቹ ምድብ የኔዋ ንብረት ቀዳሚ ሆና በመግባት አሸንፋለች።የኢትዮ ኤሌክትሪኳ አትሌት ርቀቱን ለመጨረስ 32:49.5 ፈጅቶባታል። በአሜሪካ በተካሄደው ከ20…
Read the full story at addis_news ↗