ኢሕአፓ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በምዕመናን ላይ ያነጣጠሩ የተደራጁ ጥቃቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ጠየቀ
ኢሕአፓ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በምዕመናን ላይ ያነጣጠሩ የተደራጁ ጥቃቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ጠየቀ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በእምነቱ ተከታዮችና በአገሪቱ ታሪካዊ ማንነት ላይ እየተፈጸሙ ያሉ የተደራጁ ጥቃቶችንና የጥላቻ ንግግሮችን በጽኑ እንደሚያወግዝ አስታወቀ። ፓርቲው ባወጣው መግለጫ፣ እነዚህ በቤተ ክርስቲያኒቱና በምዕመናን ላይ ያነጣጠሩ የመከፋፈልና ታሪክን የማዛባት ድርጊቶች ከተራ የአመለካከት ልዩነት ያለፉ ከባድ ሥጋቶች መሆናቸውን ገልጿል። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየተፈጸሙ ላሉ ግድያዎችና ማሳደዶች መንስኤ እየሆኑ የመጡ መሰል ድርጊቶችና ዛቻዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ኢሕአፓ በመግለጫው አሳስቧል። @Addis_News
Read the full story at addis_news ↗