ቅዱስ ሩፋኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ !
ቅዱስ ሩፋኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ ! ከአምላክ ለሰዎች የተሰጠ ፈውስ🙏 ቅዱስ ሩፋኤል ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ስሙም ከሚካኤልና ከገብርኤል ቀጥሎ በሦስተኛ ደረጃ ይቀመጣል፡፡ በመጽሐፈ ጦቢት 12÷15 “ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” ይላል፡፡ ይህ መልአክ እንደሌሎቹ ሊቃነ መላእክት ሁሉ የሰው ልጆችን ይጠብቃቸዋል፡፡ ያማልዳል፣ ከፈጣሪ ያስታርቃቸዋል፡፡ በሉቃስ 13÷6-9፣ ዘካርያስ 1÷12 እንደተጻፈው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ያለ ማቋረጥ ፈጣሪያቸው ልዑል እግዚአብሔርን ከሚያመሰግኑ ቅዱሳን መላእክት አንዱ ነው፡፡ ፈዋሴ ዱያን፡ ሕሙማንን የሚፈውስ ነው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ምድር ላይ እየተመላለሰ ሲያስተምር ድውያነ ሥጋን በተአምራት ድውያነ ነፍስን ደግሞ በትምህርቱ ይፈውስ ነበር፡፡…
Read the full story at addis_news ↗