ህገ-ወጡ ህወሃት በዚህ በሰለጠነ ዘመን በድሮ አሠላለፍ ተመልሼ ሀገር እመራለሁ በሚል ከንቱ ቅዥት በለኮሰው እሳት ተለብልቦ ጠፍቷል።
ህገ-ወጡ ህወሃት በዚህ በሰለጠነ ዘመን በድሮ አሠላለፍ ተመልሼ ሀገር እመራለሁ በሚል ከንቱ ቅዥት በለኮሰው እሳት ተለብልቦ ጠፍቷል። ይህ ቡድን ለልማት ይውል የነበረን ኢኮኖሚ የጠብመንጃ መግዣ ቢያደርገውም የገዛውም ይሁን በድጋፍ መልክ ከሴራ አቻዎቹ የተለገሠለት መሣሪያና ተተኳሽ በመከላከያ ሠራዊት እጅ ገብቷል። ይህ የጥፋት ቡድን ለእኩይ ዓላማው ማስፈፀሚያ በማዕከላዊ ዞን ጭላና በሰሜን ምዕራብ ዞን ዛና አካባቢዎች የደበቃቸው ተተኳሾችና መሣሪያዎች በሠራዊቱ የተጠናከረ ፍተሻና በህብረተሰቡ ጥቆማ በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ሥር ውሏል። 03 ፀረ-ታንክ መሳሪያ 11 ሳጥን የፀረ-ታንክ ጥይት፣ 3,060 የድሽቃ ጥይት፣ 3,000 የክላሽ ጥይት፣ 54 የሞርተር ቁምብላ፣ 01 ድሽቃ እና 10 የደረት ትጥቅ በቁጥጥር ሥር ውሏልል።
Read the full story at natnaelmekonnen21 ↗