በድሮን የተመታው የሩሲያ መርከብ እየነደደ ነው
በድሮን የተመታው የሩሲያ መርከብ እየነደደ ነው በምስራቃዊ የፊንላንድ ባህረ ሰላጤ በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) የተመታው የሩሲያ የጭነት መርከብ እሳት የማጥፋት እና የማዳን ርብርብ ቀጥሏል። ወደ ሩሲያዋ ካሊኒንግራድ ግዛት በማምራት ላይ የነበረው “ስፓርታ 2” የተሰኘው መርከብ፣ ቅዳሜ ጠዋት ከተመታ በኋላ ተንሳፎ ወደ ፊንላንድ የባህር ክልል ገብቷል። የፊንላንድ መከላከያ ኃይል ከጥቃቱ ጀርባ ዩክሬን ልትኖር እንደምትችል ቢጠቁምም፣ ኪየቭ እስካሁን በጉዳዩ ላይ በይፋ የሰጠችው አስተያየት የለም። የፊንላንድ የድንበር ጠባቂ ኃይል ከኢስቶኒያና ከሩሲያ አካላት ጋር በመተባበር መርከቡ እንዳይሰጥም ውሃ የመርጨት ሥራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ጥቃቱ በሁለት ድሮኖች መፈጸሙን የገለጹት የካሊኒንግራድ አስተዳዳሪ አሌክሲ ቤስፕሮዝቫኒክ፣ በግዛቱ የአቅርቦት ሥርዓት ላይ የተፈጠረ ስጋት እንደሌለ…
Read the full story at addis_news ↗