ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ። በCPHIA 2026 ጉባኤ ጎን ለጎን ከቡሩንዲ ፕሬዝዳንት እና የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ኤቫሪስት ንዳይሺሚዬ ጋር ውይይት አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ፤ በቅርብ ጊዜ ያደረግናቸውን ምክክሮች መሠረት በማድረግ ፣ ይህ ውይይት የጋራ ቅድሚያ የምንሰጣቸውን ጉዳዮች ለመዳሰስ፣ የሁለትዮሽ ትብብራችንን ለማስፋት እንዲሁም የጋራ ቀጣናዊ እና አህጉራዊ አጀንዳዎቻችንን ወደ ተጨባጭ ተግባራት ለመለወጥ የሚያስችሉ ሀሳቦችን እንድንለዋወጥ ዕድል ሰጥቶናል ብለዋል።
Read the full story at amharamassmedia ↗