የኢትዮጵያ የአጥንት ሕክምና ሀኪሞች ማኅበር በባለሙያዎች ቁጥር እድገት ማስመዝገቡን ገለፀ
የኢትዮጵያ የአጥንት ሕክምና ሀኪሞች ማኅበር በባለሙያዎች ቁጥር እድገት ማስመዝገቡን ገለፀ የኢትዮጵያ የአጥንት ሕክምና ሀኪሞች ማኅበር ከኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን 19ኛ ዓመታዊ ጉባኤ እና ዐውደ ርዕይ እያካሄደ ይገኛል። "የአጥንት ቀዶ ሕክምናን ማዘመን፤ ከሳይንሳዊ ትንታኔ ወደ ማኅበረሰብ ትብብር ተጽዕኖ" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ጉባኤ ላይ የማህበሩ ፕሬዝዳንት ዶክተር ኤፍሬም ገብረሃና እንደገለጹት፣ ከ10 ዓመታት በፊት በአገር አቀፍ ደረጃ ከ40 ያልበለጡ የአጥንት ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስቶች የነበሩ ሲሆን፣ አሁን ላይ በአገልግሎት ላይ የሚገኙ 463 ባለሙያዎችን እና በ13 ተቋማት በስልጠና ላይ ያሉ 327 ሐኪሞችን ጨምሮ የማኅበሩ አባላት ቁጥር 790 ደርሷል። ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ለጎረቤት አገራት የሕክምና ትምህርት ማዕከል መሆኗን…
Read the full story at addis_news ↗