የድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት የቀብር ሥነ-ሥርዓት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ

ZENA24NOWneutral2026-11-23 12:46:10 UTC
AdYour ad here[email protected]

የድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት የቀብር ሥነ-ሥርዓት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ ቅዳሜ ህዳረ 12 ቀን 2019ዓ.ም በድንገተኛ ሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው የታዋቂውና ተወዳጁ ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት የቀብር ሥነ-ሥርዓት፣ ዛሬ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅማል። በሙዚቃ ሥራዎቹና በድምፁ በበርካታ አድናቂዎቹ ልብ ውስጥ ሕያው ትዝታን ያተረፈው ሚኪያስ ቸርነት፣ ባልታሰበና ድንገተኛ ሕመም ሕይወቱ ማለፉ ቤተሰቦቹን፣ የሙዚቃውን ማኅበረሰብ እንዲሁም መላውን ወዳጅና አድናቂ በእጅጉ አሳዝኗል። ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ነበረ።ብስራት ሬድዮም ለልጆቹ፣ ለመላው ቤተሰቡ፣ ለቅርብ ወዳጆቹ እንዲሁም ለአድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል። #ዳጉ_ጆርናል

Read the full story at zena24now ↗
AdYour ad here[email protected]