በትግራይ እና ዓፋር ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ ከ12 ሰዓታት በላይ የቆየ የደን ቃጠሎ ጉዳት አደረሰ።

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-09-01 15:35:01 UTC
AdYour ad here[email protected]

በትግራይ እና ዓፋር ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ ከ12 ሰዓታት በላይ የቆየ የደን ቃጠሎ ጉዳት አደረሰ። ቃጠሎው ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. በትግራይ ምሥራቃዊ ዞን፣ ፃዕዳ እምባ ወረዳ፣ ከዓፋር ክልል ዳሉል ወረዳ ጋር በሚዋሰነው የሐዊለ ቀበሌ አካባቢ መነሳቱን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል። በእሳቱ 4.125 ሄክታር የሚገመት ደንና የግጦሽ ሳር መውደሙ ተገልጿል። በተለይም የገራህቲ ጥብቅ ደን በቃጠሎው ጉዳት ደርሶበታል። የቃጠሎው መንስኤ እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን፣ ምክንያቱን ለማጣራት ምርመራ መጀመሩ ታውቋል። የትግራይ ክልል ምሥራቃዊ ዞን አስተዳደር እንዳስታወቀው በአካባቢው ነዋሪዎች ባህላዊ የእሳት ማጥፊያ ዘዴዎች በመጠቀም ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 5፡30 ላይ ቃጠሎው ሙሉ በሙሉ ማስቆም ተችሏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]