መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሥራ ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቀቀ

ADDIS_NEWSneutral2026-11-24 08:15:11 UTC
AdYour ad here[email protected]

መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሥራ ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቀቀ መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ በቅርቡ የሲሚንቶ ምርትና ሽያጭ እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡ ፋብሪካው በይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ መሠረት፣ ከሲሚንቶ ንግድ ጋር የተያያዘ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ደንበኞች ከ400 ኩንታል በላይ ሲሚንቶ በቀጥታ ከፋብሪካው መግዛት ይችላሉ። አያይዞም በብዛት «ፒፒሲ» (PPC) ሲሚንቶ ለሚገዙ ደንበኞች ልዩ የዋጋ ቅናሽ መደረጉን የገለጸው ፋብሪካው፣ ደንበኞች ይህንን ምቹ አጋጣሚ እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርቧል። @Addis_News @Addis_News

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]