በአንድ ወር ከ66 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
በአንድ ወር ከ66 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2019 በጀት ዓመት ጥቅምት ወር ብቻ 66 ሺህ 473 አዳዲስ ደንበኞችን ከኤሌክትሪክ መረብ ጋር በማገናኘት የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል። ተቋሙ በወሩ 88 ሺህ 253 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ዕቅድ ይዞ የነበረ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 66 ሺህ 473 ደንበኞችን በማገናኘት የዕቅዱን 75.3 በመቶ ማሳካት ችሏል። የወሩ አፈጻጸም ከ2018 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 20 ሺህ 23 ተጨማሪ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ያሳያል። በ2018 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወር 46 ሺህ 450 ደንበኞች አገልግሎቱን ያገኙ ነበር። በወሩ አዲስ ከኤሌክትሪክ መረብ ከተገናኙት ደንበኞች መካከል 62 ሺህ 574 (94.1 በመቶ) የቅድመ ክፍያ…
Read the full story at zena24now ↗