መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሥራ ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቀቀ
መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሥራ ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቀቀ መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ በቅርቡ የሲሚንቶ ምርትና ሽያጭ እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡ ፋብሪካው በይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ መሠረት፣ ከሲሚንቶ ንግድ ጋር የተያያዘ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ደንበኞች ከ400 ኩንታል በላይ ሲሚንቶ በቀጥታ ከፋብሪካው መግዛት ይችላሉ። አያይዞም በብዛት «ፒፒሲ» (PPC) ሲሚንቶ ለሚገዙ ደንበኞች ልዩ የዋጋ ቅናሽ መደረጉን የገለጸው ፋብሪካው፣ ደንበኞች ይህንን ምቹ አጋጣሚ እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርቧል። ======================== ለትክክለኛ ወቅታዊ መረጃ ቻናላችንን join አድርጉ፣ለትክክኛ መረጃ ፈላጊዎች ጋብዙ👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
Read the full story at ayuzehabeshanews ↗