ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለሱዳን ወገኖች ወደ ውይይት ጠረጴዛ እንዲመጡ ጥሪ አቀረቡ‼

WASULIFEneutral2026-11-24 15:47:33 UTC
AdYour ad here[email protected]

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለሱዳን ወገኖች ወደ ውይይት ጠረጴዛ እንዲመጡ ጥሪ አቀረቡ‼ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በሱዳን ያለውን ጦርነት ለማስቆም እና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ሁሉም የሱዳን ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ሲቪል አካላት ኢትዮጵያ በምታዘጋጀው ሁሉን አቀፍ የውይይት መድረክ ላይ እንዲሳተፉ ይፋዊ ጥሪ አቀረቡ። ​ጠቅላይ ሚኒስትሩ አራተኛ ዓመቱን የያዘው የሱዳን ጦርነት ያስከተለው ሰብዓዊ ቀውስና ውድመት የኢትዮጵያን ሕዝብ ሕሊና የሚነካ ቁስል መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከማንኛውም የተለየ የፖለቲካ አጀንዳ ነጻ በመሆን እና ከሁሉም ወገኖች እኩል ርቀት ላይ በመቆም፣ ሱዳናውያን ያለ ውጭ ጣልቃ ገብነት በራሳቸው ፍላጎት ተወያይተው የብሔራዊ አንድነት መንግሥት የሚመሠርቱበትን መድረክ እንደምታመቻች አረጋግጠዋል። ​በመጨረሻም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና ወዳጅ ሀገራት ለሱዳን…

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]