በወሲባዊ ትንኮሳ ወንጀል የተጠረጠሩት የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ከስልጣን እንደሚለቁ ተገለፀ
በወሲባዊ ትንኮሳ ወንጀል የተጠረጠሩት የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ከስልጣን እንደሚለቁ ተገለፀ የአሜሪካ የኮንግረስ አባል ጂሚ ጎሜዝ፣ በሠራተኛቸው ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ ፈጽመዋል የሚል አሳማኝ ማስረጃ መገኘቱን የኮንግረሱ ሥነ ምግባር ኮሚቴው ካስታወቀ በኋላ ከሥልጣናቸው ሊለቁ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የካሊፎርኒያ ዴሞክራት የሆኑት ጎሜዝ፣ በሠራተኛቸው ላይ ያልተፈለገ የወሲብ ግንኙነት ጥያቄ ማቅረባቸውን ኮሚቴው በሪፖርቱ ገልጿል። ጎሜዝ የኮሚቴውን ውሳኔ ባይቀበሉም በትዳራቸው ላይ ለፈጸሟቸው የግል ስህተቶች ኃላፊነት እንደሚወስዱ ገልጸዋል። የ51 ዓመቱ የምክር ቤት አባል፣ ከሳምንት በኋላ ከሥልጣናቸው እንደሚለቁ ይጠበቃል። የሥነ ምግባር ኮሚቴው በቀጣይ ሳምንት የምርመራ ሂደቱን ለማፋጠን ስራዎችን ማጠናከሩ ተዘግቧል። በቤዛዊት አራጌ #ዳጉ_ጆርናል
Read the full story at zena24now ↗