ቀድሞ ይሠራበት ከነበረው ድርጅት መኪና በመስረቅ የተጠረጠረው ግለሰብ በፖሊስ እየተፈለገ ነው ተባለ

ZENA24NOWneutral2026-11-25 09:33:48 UTC
AdYour ad here[email protected]

ቀድሞ ይሠራበት ከነበረው ድርጅት መኪና በመስረቅ የተጠረጠረው ግለሰብ በፖሊስ እየተፈለገ ነው ተባለ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከሚገኘው የቱሉ ቦሎ ኬላ የመንገድ ሥራ ድርጅት ካምፕ የተሰረቀው ፒክአፕ ተሽከርካሪ፣ በፖሊስ ክትትል በአዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ መገኘቱን የክልሉ ፖሊስ አስታውቋል። የክልሉ ፖሊስ የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-62192 አ.አ የተመዘገበው ተሽከርካሪ መሰረቁ ከታወቀ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ፖሊስ ክትትል ጀምሯል። ተጠርጣሪው ክትትል እየተደረገበት መሆኑን ሲያውቅ መኪናውን በቃሊቲ አካባቢ አቁሞ ከቦታው መሰወሩን ኮማንደሩ ገልጸዋል።ተሽከርካሪው ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም. ጠዋት ከድርጅቱ ካምፕ የተወሰደ ሲሆን፣ ተጠርጣሪው ወንድወሰን ማሞ ቀደም ሲል በድርጅቱ…

Read the full story at zena24now ↗
AdYour ad here[email protected]