በትግራይ ከእስር ያመለጠ ግለሰብ በአንድ ወር ውስጥ አምስት ሴቶችን በመግደል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ዋለ
በትግራይ ከእስር ያመለጠ ግለሰብ በአንድ ወር ውስጥ አምስት ሴቶችን በመግደል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ዋለ በትግራይ ክልል ከዓመታት በፊት በአንዲት ሴት ግድያ ተከሶ የ22 ዓመት እስራት የተፈረደበት ግለሰብ፣ ከእስር ከወጣ በኋላ አምስት ሴቶችን አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በመግደል መጠርጠሩን የሰሜን ምዕራብ ዞን ወንጀል ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ገብረሥላሴ አማረ ገለጹ። የ54 ዓመቱ ተጠርጣሪ ተስፋይ ገብረዮሐንስ አምስቱንም ሴቶች ከገደለ በኋላ በሟቾቹ ላይ ፆታዊ ጥቃት እንደፈጸመ ኮማንደሩ ገልጸዋል። ተጠርጣሪው ከአምስቱ መካከል የአንዲትን ሟች የአምስት ዓመት ልጅንም ማገቱን ፖሊስ አስረድቷል። በመስከረም ወር አጋማሽ በትግራይ ኃይሎች እና በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት መካከል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ የትግራይ ኃይል እስረኞችን ለቋል ያሉት ኮማንደሩ ተጠርጣሪው በዚህ አጋጣሚ ከእስር…
Read the full story at addis_news ↗