#ጥቆማ
#ጥቆማ በኢትዮጵያ የጃፓን ኤምባሲ እሁድ ኅዳር 20 ቀን 2019 ዓ.ም. በጁቬንቱስ ክለብ በሚካሄደው "የጃፓን የባህል ቀን" ላይ ለሚደረገው የማንጋ (Manga) የሥዕል ውድድር የምዝገባ ጥሪ አቅርቧል። በዕለቱ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት በሚካሄደው ውድድር ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በላይ የሆኑ ጀማሪና ሙያተኛ ሰዓልያን ይሳተፋሉ። የምዝገባ የመጨረሻ ቀን አርብ ኅዳር 18 ቀን 2019 ዓ.ም. ነው ተብሏል። ተወዳዳሪዎች ከ"የጃፓን ምግብ"፣ ከ"የጃፓን የማርሻል አርት" ወይም ከ "ሜካ እና ሳይንስ ልብወለድ" (ለምሳሌ ሮቦቶች) አንዱን መርጠው በአንድ ገጽ የመሳያ ወረቀት ላይ ይሥላሉ። የራስን ገጸ-ባህሪያት መፍጠር ወይም ነባር ገጸ-ባህሪያትን በፈጠራ ትርጓሜ መጠቀም ይቻላል፤ ነገር ግን ሥዕሎችን በቀጥታ መገልበጥ ወይም ለሁሉም ዕድሜ የማይመጥን ይዘት ማካተት አይፈቀድም። የተቀደደ…
Read the full story at tikvahethmagazine ↗