በጠለምት ወረዳ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሰው ሕይወት አለፈ፤ ከ2 ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቀሉ

ADDIS_REPORTERneutral2026-09-02 08:22:20 UTC
AdYour ad here[email protected]

በጠለምት ወረዳ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሰው ሕይወት አለፈ፤ ከ2 ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቀሉ ​በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ “ግልቤና” ቀበሌ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በደረሰ ከባድ የመሬት መንሸራተት አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ፣ በአራት ሰዎች ላይ ደግሞ አካል ጉዳት ደርሷል። ​በአደጋው ሳቢያ 411 አባወራዎች ወይም ከ2,000 በላይ የቤተሰብ አባላት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል። በተጨማሪም 26 መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ የተደረመሱ ሲሆን፣ 31 የቤት እንስሳትም ሞተዋል። ​የመሬት መንሸራተቱ አሁንም እየተስፋፋ ቢሆንም፣ ሕዝቡ ቀድሞ ወደ ቀበሌው ማእከል እንዲወርድ በመደረጉ ተጨማሪ የሰው ሕይወት ማዳን ተችሏል። ​ተፈናቃዮቹ በአሁኑ ወቅት በቀበሌው ማእከል ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን፣ አስቸኳይ የምግብና የቁሳቁስ እርዳታ የሚፈልጉ ቢሆንም እስካሁን ምንም ዓይነት…

Read the full story at addis_reporter ↗
AdYour ad here[email protected]