የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተና!
የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተና! ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቃችሁ የጤና ባለሙያዎች በታህሳስ ወር 2019 ዓ.ም የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተና ለመስጠት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ በመሆኑም መረጃችሁን ከዚህ ቀደም ወደ ሲስተም ያላስገባችሁ ነባር እና አዲስ ተመዛኞች ከህዳር 21-30/2019 ዓ.ም ድረስ ብቻ https://hple.moh.gov.et/ ላይ በመግባት የብሔራዊ መታወቂያ መለያ ቁጥር (16 Digit) በማስገባት አስፈላጊ መረጃዎችን በማሟላት ለምዝገባ እንድትዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል። ይህ መረጃን የማስተሳሰር ሒደት እንዳለቀ የፈተና ጣቢያ መረጣ ሒደት እንደሚቀጥል ተገልጿል። የመውጫ ፈተና ተፈትናችሁ ያለፉችሁና ስማችሁ ወደ ሲስተም ያልገባላችሁ ተመዛኞች ስማችሁን በተማራችሁበት ተቋም አማካኝነት ወደ ሲስተም ማስጫን ይጠበቅባችኋል ተብሏል።…
Read the full story at tikvahuniversity ↗