በጋምቤላ ክልል የተከሰተው የዝናብ እጥረት በሰብል ምርታማነት ላይ ስጋትን ደቀነ
በጋምቤላ ክልል የተከሰተው የዝናብ እጥረት በሰብል ምርታማነት ላይ ስጋትን ደቀነ በጋምቤላ ክልል የሚገኙት አብዛኛዎቹ አካባቢዎች በዘንድሮው የክረምት ወቅት በቂ ዝናብ ባለማግኘታቸው ሁኔታው በሰብል ዕድገትና ምርታማነት ላይ ስጋት መፍጠሩን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል ። የቢሮው ኃላፊ አቶ አንድሪው ቱት ለብስራት ሬድዮ እንደገለጹት፣ የዝናብ እጥረቱን ተከትሎ በሰብሎች ዕድገት ላይ ጉዳት አጋጥሟል። ይህም በቀጣይ በምርት መጠንና ጥራት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል ነው ያሉት። የዝናብ እጥረቱ በተለይም ኢታንግ ልዩ ወረዳን ጨምሮ በኑዌር ብሔረሰብ ዞንና በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች መከሰቱንም ጠቁመዋል። በክልሉ የተከሰተው የዝናብ እጥረት በሰብሎች የዕድገት ደረጃ ላይ ልዩነት በመፍጠር የምርት ቅነሳ አደጋን ሊያባብስ እንደሚችል የተናገሩት ሀላፊው…
Read the full story at zena24now ↗