የትግራይ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ በክልሉ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞችና አመራሮች የትምህርት መረጃዎችና ሰነዶች እንዲጣሩ አዘዘ።

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-11-28 19:25:01 UTC
AdYour ad here[email protected]

የትግራይ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ በክልሉ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞችና አመራሮች የትምህርት መረጃዎችና ሰነዶች እንዲጣሩ አዘዘ። ቢሮው ለሁሉም የክልሉ የመንግሥት ተቋማት በላከው ደብዳቤ የሠራተኞችና የአመራሮች የትምህርት መረጃና ሰነዶች እስከ ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም. ተጣርተው እንዲቀርቡለት አዟል። አንዳንድ የመንግሥት ሠራተኞችና አመራሮች ሕገወጥ የትምህርት መረጃና ሰነዶችን በመጠቀም በሥራ ላይ እንደሚገኙ የገለጸው ቢሮው፣ የተጭበረበሩ ሰነዶችን ከእውነተኛዎቹ መለየት እንዳለበት አሳስቧል። በመሆኑም፦ - ቢሮዎች፣ - ዘርፎች፣ - ክፍለ ከተሞች፣ - ሆስፒታሎች፣ - ኮሌጆች በሥራቸው የሚገኙ ሠራተኞችና አመራሮች የትምህርት መረጃና ሰነዶች በአስቸኳይ እንዲያጣሩ ጥብቅ መመሪያ ተላልፏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ህዳር 19 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]