👏 #ዶክተር_እጹብ_ስንታየሁ

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-11-28 22:03:07 UTC
AdYour ad here[email protected]

👏 #ዶክተር_እጹብ_ስንታየሁ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ካስመረቃቸው የሕክምና ዶክተሮች መካከል ዶክተር እጹብ ስንታየሁ 3.86 ከ4.00 ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በሜዳሊያ ተመርቃለች። ዶክተር እጹብ የተማሪነት ጉዞዋን በከፍተኛ ውጤት ማጠናቀቋ የልፋቷን ዋጋ ያገኘችበት እና ትልቅ ደስታ የተሰማት አጋጣሚ መሆኑን ገልጻለች። " 3.86 በሕይወቴ ትልቅ ትርጉም ፈጥሮ ሕይወት ለማዳን አዘጋጅቶኛል " ያለችው ዶክተር እጹብ፣ የትምህርት ጉዞዋ በኮቪድ-19 ወረርሽኝና በተለያዩ ፈተናዎች የታጀበ ቢሆንም በዚያው ወቅት ብዙ ዕውቀትና ልምድ ማግኘት እንደቻለች ተናግራለች። " የሕክምና ሙያ የሰውን ሕይወት በማዳን ፣ በማከምና በማገልገል ላይ የተመሠረተ ነው " ያለች ሲሆን ከዚህ በኋላ ሕዝብን በማገልገልና የሀገርን አደራ በመወጣት ለሙያው ያላትን ቁርጠኝነት ገልጻለች።…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]