ከመንግሥትና ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ፈቃድ ውጭ የመማሪያ መጽሐፍትን ማተምና ለንግድ ማዋል ተከለከለ

ADDIS_NEWSneutral2026-11-29 11:32:53 UTC
AdYour ad here[email protected]

ከመንግሥትና ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ፈቃድ ውጭ የመማሪያ መጽሐፍትን ማተምና ለንግድ ማዋል ተከለከለ የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር የመማሪያና የማስተማሪያ መጽሐፍትን ዝግጅት፣ ሕትመት፣ ስርጭትና አጠቃቀም በአንድ ወጥ አሠራር ለመቆጣጠር ያወጣው አዲስ መመሪያ ቁጥር 1163/2019 ይፋ ሆነ። በመመሪያው መሠረት ከሚኒስቴሩ ወይም ከሚመለከተው የክልል ትምህርት ቢሮ የጽሑፍ ፈቃድ ውጭ ማንኛውንም የመማሪያና የማስተማሪያ መጽሐፍ ማተም፣ ማባዛትና ለንግድ ዓላማ ማዋል ተከልክሏል። በትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተፈረመው መመሪያው፣ በፌዴራልና በክልል የመንግሥትና የግል ትምህርት ተቋማት እንዲሁም በውጭ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል። በመመሪያው መሠረት ተማሪዎች የተረከቡትን መጽሐፍ ቢያጡ ወይም ለመማር በማይችሉበት ደረጃ ቢያበላሹ፣…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]