የሕዳር ፅዮንን በዓል ለማክበር እንግዶች ወደ አክሱም ከተማ እየገቡ ነው።
የሕዳር ፅዮንን በዓል ለማክበር እንግዶች ወደ አክሱም ከተማ እየገቡ ነው። ነገ የሚከበረውን የሕዳር ፅዮን በዓል ለማክበር ምዕመናን ከትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ፣ ከኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎችና ከውጭ ሀገራት የመጡ እንግዶች በሁሉም አቅጣጫ ወደ አክሱም ከተማ እየገቡ ይገኛሉ። የከተማዋ ወጣቶች ጥንታዊ ትውፊትንና ሃይማኖታዊ ክብርን በጠበቀ መልኩ እንግዶቹን እግራቸውን በማጠብና ቁርስ በማቅረብ በታላቅ ትህትና እየተቀበሏቸው ሲሆን እንግዶቹም ለተደረገላቸው ፍቅር የተሞላበት አቀባበል ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ሕዳር 20 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
Read the full story at tikvahethiopia ↗